የፌጦ የጤና በረከቶች‼️ #ጤና #ፌጦ #Feto
የፌጦ የጤና በረከቶች ፌጦ በሳይንሳዊ ስሙ (Lepidium sativum) እየተባለ ይጠራል። የዚህ ተክል ቅጠል እና ዘር ባክቴሪያዎችን እና ቫይረሶችን ለመከላከል የሚረዱ ኬሚካሎችን በውስጣቸው እንደያዙ የጤና መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ፌጦ ኢትዮጵያን ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በሕንድ በአውሮፓ፣ በደቡብ ምዕራብ እስያ እና በግብፅ የሚገኝ ተክል ሲሆን በባህላዊና በዘመናዊ መንገድ የተለያዩ በሽታዎችን ለመከላከል ጥቅም ላይ እንደሚውል የሄልዝ ላይን የጤና መረጃ ያመለክታል። ፌጦ በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ መጠሪያዎች እንዳሉትም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ለአብነትም ሃሊም ፣ ቻንድራሱራ እና ሆላን በመባል ይጠራል። ፌጦ ለጤና በርካታ ጥቅሞችን ይሰጣል።ከእነዚህም መካከል ፦ 1.. ደም መርጋትን ይከላከላል ፌጦ በካሎሪ ይዘቱ ዝቅተኛ ቢሆንም በንጥረ ነገሮች የተሞላነው።በውስጡ ካርቦሃይድሬት፣ፕሮቲን:፣ፋይበር:፣ፖታስየም፣ቫይታሚን ኤ፣ቫይታሚን ሲና ቫይታሚን ኬ ይይዛል፡፡ የጤና መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ፌጦ የደም መርጋትን ለመከላከል ያስችላል። 2. የአጥንት ጤንነትን ይጨምራል ፌጦ በከፍተኛ ሁኔታ በቫይታሚን ኬ የበለጸገ ስለሆነ አጥንት ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ 3. የበሽታ መከላከል አቅምን ይጨምራል በቫይታሚን ሲ የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅም ለማሻሻል ይረዳል። ስለሆነም ፌጦ ጥሩ የቫይታሚን ሲ ምንጭ በመሆኑ የበሽታ ስጋትን በመቀነስ በሽታን የመከላከል አቆምን ይጨምራል፡፡ 4. ክብደትን ለመቀነስን ይረዳል ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከፍተኛ የካሎሪ መጠ...