የፌጦ የጤና በረከቶች‼️ #ጤና #ፌጦ #Feto
የፌጦ የጤና በረከቶች
ፌጦ በሳይንሳዊ ስሙ (Lepidium sativum) እየተባለ ይጠራል። የዚህ ተክል ቅጠል እና ዘር ባክቴሪያዎችን እና ቫይረሶችን ለመከላከል የሚረዱ ኬሚካሎችን በውስጣቸው እንደያዙ የጤና መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ፌጦ ኢትዮጵያን ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በሕንድ በአውሮፓ፣ በደቡብ ምዕራብ እስያ እና በግብፅ የሚገኝ ተክል ሲሆን በባህላዊና በዘመናዊ መንገድ የተለያዩ በሽታዎችን ለመከላከል ጥቅም ላይ እንደሚውል የሄልዝ ላይን የጤና መረጃ ያመለክታል።
ፌጦ በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ መጠሪያዎች እንዳሉትም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ለአብነትም ሃሊም ፣ ቻንድራሱራ እና ሆላን በመባል ይጠራል።
ፌጦ ለጤና በርካታ ጥቅሞችን ይሰጣል።ከእነዚህም መካከል ፦
1.. ደም መርጋትን ይከላከላል
ፌጦ በካሎሪ ይዘቱ ዝቅተኛ ቢሆንም በንጥረ ነገሮች የተሞላነው።በውስጡ ካርቦሃይድሬት፣ፕሮቲን:፣ፋይበር:፣ፖታስየም፣ቫይታሚን ኤ፣ቫይታሚን ሲና ቫይታሚን ኬ ይይዛል፡፡
የጤና መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ፌጦ የደም መርጋትን ለመከላከል ያስችላል።
2. የአጥንት ጤንነትን ይጨምራል
ፌጦ በከፍተኛ ሁኔታ በቫይታሚን ኬ የበለጸገ ስለሆነ አጥንት ጠንካራ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
3. የበሽታ መከላከል አቅምን ይጨምራል
በቫይታሚን ሲ የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅም ለማሻሻል ይረዳል።
ስለሆነም ፌጦ ጥሩ የቫይታሚን ሲ ምንጭ በመሆኑ የበሽታ ስጋትን በመቀነስ በሽታን የመከላከል አቆምን ይጨምራል፡፡
4. ክብደትን ለመቀነስን ይረዳል
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከፍተኛ የካሎሪ መጠን ያላቸውን ምግቦች ዝቅተኛ የካሎሪ መጠን ባላቸው ምግቦች መተካት የካሎሪ መጠንን ለመቀነስ ይረዳል።
ስለዚህ ፌጦ እና ሌሎች ብዙ ስታርች የሌላቸው አትክልቶች በተፈጥሮ ዝቅተኛ የካርቦሃይድሬት መጠን ስላላቸው ክብደትን ለመቀነስ ይጠቅማሉ፡፡ ምክንያቱም የካሎሪ እና የካርቦሃይድሬት ይዘታቸው ዝቅተኛ ስለሆነ፡፡
5. ከመርዛማ ነገሮች ይከላከላል
እንደ አሉሚኒየም ያሉ ከባድ ብረቶችን የያዙ ነገሮችን በእለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ ልናገኛቸው እንችላለን፡፡ለአብነትም በመዋቢያዎች፣በመድሃኒቶች፣ በክትባቶች እና በጭስ ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው።
አሉሚኒየም በሰውነት ሕብረ ሕዋሳት ውስጥ ስለሚከማች፣ እንደ ኦክሳይድ ውጥረት እና ደካማ የጉበት ተግባር እንዲኖር ያደርጋል፡፡
ስለዚህ ፌጦን መመገብ እንደነዚህ አይነት መርዛማ ነገሮችን ለማስወገድ ያግዛል።
6. ልብን ከበሽታ ለመከላከል ይጠቅማል።
ፌጦ ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ አሲዶችን ማለትም ፋቲ አሲድ፣አስፓርቲክ አሲድ፣ግሉታሚክ አሲድ፣ሊኖሊክ አሲድ ፣ ኦሊክ አሲድና ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ያሉት በመሆኑ ደም ግፊትን ይቀንሳል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን ያጠናክራል፣የአእምሮ እና የልብ ጤናን ይጠብቃል።
7. የስኳር በሽታን ለመቆጣጠር ይረዳል
ፌጦ የስኳር በሽታን በመቆጣጠር የደም ስኳር መጠን ለመቀነስ ይረዳል::
8. ካንሰርን ይከላከላል
ፌጦ ብዙ የፀረ-ካንሰር ጥቅሞች እንዳሉት ጥናቶች ያመላክታሉ።
ፌጦን በአመጋገባችን ውስጥ በጨመርን ቁጥር በሰውነታችን ውሶጥ ህይወት ያላቸው የካንሰር ሕዋሳት መጠን እየቀነሱ እና የጤናማ ሴሎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚሄድ ነው የጤና መረጃዎች የሚጠቁሙት።
9. የአይን ጤንና ያሻሽላል፡፡
ፌጦ በአንፃራዊነት በቫይታሚን ኤ የበለፀገ ስለሆነ ዝቅተኛ የብርሃን እይታን ለማስተካከልና ጤናማ እይታ እንዲኖረን ያደርጋል።
10. የጡት ወተት ምርትን ይጨምራል፡፡
ፌጦ ለጡት ወተት እና ለጡት ቲሹ እድገት አስፈላጊ የሆኑ ቪታሚኖች እና ማዕድናት እንደሚይዝ በጥናት መረጋገጡን የሄልዝ ላይን መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም ፕላላቲን የተባለውን ወተትን ለማምረት የሚያስችለውን ሆርሞን ለማነቃቃት ስለሚያገለግል በተለይ የሚያጠቡ እናቶች ፌጦን መመገብ እንደሚገባቸው የጤና መረጃዎች ይመከራሉ።
በተጨማሪም ፌጦ ለሳል፣ ለተቅማጥእና ለሆድ ድርቀት ህክምና እንደሚያገለግል የጤና መረጃዎች ያስረዳሉ።
ምንጭ፡- ከHealth line ወስዶ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እንደዘገበው
Thank you for the information
ReplyDelete