ከዚህ ተፈጥሯዊ ትስስር ማምለጥ አይቻልም። #ቀይ_ባህር
ቀይ ባህር የክፍፍል አጀንዳ ሳይሆን ኢትዮጵያና ኤርትራን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሀገራትን በኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን በማህበራዊና ፖለቲካዊ መስኮች የሚያስተሳስር ተፈጥሮአዊ (ጂኦግራፊያዊ) ገፅታ ነው!
ነገር ግን አንድ ነገር ማድረግ ይቻላል ፤ ይገባልም። እሱም በምን አይነት መልኩ ከዚህ ተፈጥሯዊ ትሩፋት ሰላማዊ ፣ ህጋዊና ወንድማዊ በሆነ አግባብ መጠቀም እንችላለን ብለን በመወያየት ለሁሉም ሀገራት የጋራ ጥቅም በሚውል መልኩ መጠቀም ይቻላል። የቀይ ባህር አጀንዳ ለኢትዮጵያም ሆነ ለኤርትራ የሆኑ የፖለቲካ ሀይሎች ጉዳይ ሳይሆን የሀገራት " ብሄራዊ ጥቅም" ነው። ብሄራዊ ጥቅም ደግሞ የሆኑ የፖለቲካ ሀይሎች ወደ ስልጣን ቢወጡም፣ ከስልጣን ቢወርዱም የማይቆምና የማይቋረጥ የሀገራት የህልውና ጉዳይ ነው።
ቀይ ባህር በሀገራት መካከል የረጅም ጊዜ የእርስ በርስ መስተጋብር ታሪክ ያለው ቢሆንም የተለያዩ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የባህል ሥርዓቶች ለላቀ ቅንጅት እንዳያገለግል ተግዳሮት ሆኖበታል። ይባስ ብሎም በተለይም የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ባህል ቀይ ባህርን ሀገራትን እንደሚያስተሳስር ጂኦግራፊያዊ ገፅታ ሳይሆን እንደ መለያየት መስመር እንዲውል ሲያደርግ ቆይቷል። ይህ አዙሪት አብቆቶ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ መካከል ዘላቂ የጋራ ጥቅም እንዲሆን ቢደረግ በሁለቱ ሀገራት መካከል አዎንታዊ ሰላም እንድሰፍን በጎላ አስተዋጽኦ ከመጫወቱም አልፎ ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠና መረጋጋት አይነተኛ ሚና ሊጫወት ይችላል።
በዶ/ር ሚኤሳ ኤለማ
Comments
Post a Comment