የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ ይሰጣል

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ታህሳስ 12//04/2016 ዓ.ም ሊሰጥ ለነበረው የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ለመፈተን በስፍራው ለተገኛችሁ እና የከተማ አስተዳደሩን አቅጣጫ በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በመቀበል ውሳኔውን ላከበራችሁ ሰራተኞች በሙሉ የላቀ ምስጋናውን እያቀረበ ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ ይጠይቃል።
በቀጣይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑንም ቢሮው ያስታውቃል።

የከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ለአመራሮች ፣ ለባለሙያዎች እና ለሰራተኞች ፈተና እንዲሰጡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነት በመስጠት ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ቀን ማለትም በ 12/04/2016 ዓ.ም ፈተና ለመፈተን ሙሉ ዝግጅቱን ቢያጠናቅቅም ፈተናው የ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ባጋጠመው ቴክኒካል ችግር ምከንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በእለቱ ከረፋዱ 5:00-11:30 በፍጹም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እና በትእግስት የፈተናውን መሰጠት ስትጠባበቁ ለነበራችሁ የ ከተማ አስተዳደሩ ሰራተኞች በሙሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የላቀ ምስጋናውን እያቀረበ ነገር ግን በእለቱ በሰራተኛው ላይ ለደረሰው መጉላላት እና እንግልት ሁሉ ይቅርታ ይጠይቃል።
በተያያዘም ተፈታኞች በተረጋገጠ ሰላም አና በተረጋጋ ስሜት ፈተናውን እንዲወስዱ የተለመደ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ላሳየው እና የሰላም አርበኛ ለሆነው የመንግስት ሰራተኛ በሙሉ ቢሮው ምስጋናን ይቸራል።
በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩን አቅጣጫ በመቀበል የትራንስፖርት አቅርቦት በማመቻቸት፣የትራንስፖርት ፍሰቱን በማሳለጥ እና ሰላም እና ፀጥታን በማስጠበቅ ሙሉ ድጋፍ ላደረጋቸው ባለድርሻ አካላት በሙሉ ቢሮ ከፍ ያለ ምስጋናውን ያቀርባል።
በቀጣይም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እያስታወቀ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም በ ኦረንቴሽን ወቅት የተቀመጡ መስፈርቶችን በሙሉ አሟልተው ለፈተና እንዲገኙ ቢሮው ጥሪ ያቀርባል።
በተመሳሳይም የተዘጋጀው ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በመሰረዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይቅርታ መጠየቁም አይዘነጋም።


Comments

Popular posts from this blog

Jobs at Your Fingertips: Ethiopia's Game-Changing Labor Market Platform #LMIS

የፌጦ የጤና በረከቶች‼️ #ጤና #ፌጦ #Feto

Ethiopia on the Rise: Beyond the BRICS Spotlight #BRICS+ #Ethiopia